Take a fresh look at your lifestyle.

ጃዋር መሃመድ ኦህዴድ የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ ይመልሳል የሚል እምነት እንደሌለው ይናገራል

ከትላንት በስትያ ከአቶ ማሞ ገዳ ( አባ ወሌንሶ ) ጋር ሆነን አቶ ጃዋር መሀመድን አግኝተነው ነበር ። አቶ ማሞ ገዳ በ1980 ዎቹ መጨረሻ የኦሮሞን ህዝብ የትግል ዘፈን በካሴት ያሳተሙ ሰው በዚህም ተያይዞ በወለጋ የኦነግ የፓለቲካ ክፍል ሀላፊ ሆነው እስከ 1990 የሰሩ በመጨረሻም ወያኔ ኦነግን ከሀገር ሲያሰድደው በአቶ ስለሺ ጎዴ የሚመራው ኦህዴድ እጃቸውን ይዞ ለወያኔ በማስረከቡ ለ6 ዓመታት በእስር አሳልፈዋል ። አቶ ማሞ በ1997 ኦፌኮን ወክለው በምስራቅ ሸዋ ዞን በቦሰት ወረዳ ምርጫ አሸንፈው የፓርላማ አባል ሆነው አገልግለዋል ።

ጃዋር ሳገኘው ያው ጃዋር ሆኖ ነው ያገኘውት ከኢንተርኔቱ አለም እና ከቴሌብዥን ኢንተርቪው የተለየ ሰው አይደለም ሰማይ የነካ በራስ መተማመን ያለው ሰው ሆኖ አግንቼዋለው ። ትግሉ እንዳልተጠናቀቀ ያምናል አሁን መጣ እሚባለውን ለውጥ በጥርጣሬ እያየ ይገኛል ፣ዴሞክራሲ ሊባል እሚችለው አለ በምርጫ ተፈትሾ ህዝባችብ የፈለገውን መምረጡን ስናረጋግጥ ነው ለውጥ መሆኑን እምነን ምንቀበለው ሲል ሰምቼዋለው ፣ ኦፌኮን እና ኦነግን ለማዋሀድ በሰፊው እየሰራ እንደሆነ እና ለኦሮሞ ህዝብም የእነሱ ወደ አንድነት መምጣት የወደፊቱን መፃዒ እድል ይወስነዋል ብሩህም ያደርገዋል ብሎ ያምናል ።

ኦህዴድ የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ ይመልሳል የሚል እምነት እንደሌለው ይናገራል በእርግጥ ይህን ነገር ባለፈው ከዶ/ር መራራም ስናወራ የኦህዴድ የአሁኑ ፓለቲካ የሰሜን ፓለቲካ ነው ሲሉ ሰምቻለው ። የጃዋር ዕቅድ እና ግብ አድርጎ እየሰራ ያለው በ2012 ኦህዴድን በምርጫ በክልሉ መዘረር ይመስለኛል በእርግጥ እንዲህ ሲል አልሰማውም ነገር ግን ሀሳቡ ያ ይመስላል በንግግሩ ። ጃዋር እራሱን ባጠቃላይ የብሔር ብሔረሰብ ዋስ ጠበቃ አድርጎ እሚመለከት ሰው መስሎ ታይቶኛል ወሬው ሁሉ ስለ ብሔረሰቦች መብት ስለሆነ ብዬ ነው ያንን ያልኩት ። ጠቅልዬ ልግዛ እሚሉት ጋቢ ለደርግም አልበጀውም ስለዚህ ሀገሪቱ ከፌደራሊዝም ውጪ ልከተል ካለች አደጋው የሰፍ እንደሆነ በሰፊው ያብሯሯል ። ባጠቃላይ ጃዋር ውስብስብ ከሆነው ከብሔር ፓለቲካ ውጪ ሌላ መድሀኒት ያለ እሚመስለው ሰው መስሎ አልታየኝም ።

ጃዋርን ዝም ብለህ ሲናገር ስታየው መደራጀት የሞት የሽረት ጉዳይ መስሎ ይታይሀል ።(በዘውዳለም ታደሰ)

Leave A Reply

Your email address will not be published.