Take a fresh look at your lifestyle.

አምባሳደር ዘውዴ ረታ ማን ናቸው?

አምባሳደር ዘውዴ ረታ በአዲስ አበባ ነሐሴ 7 ቀን 1927 ዓ.ም. ልዩ ስሙ ኦርማ ጋራዥ አካባቢ ተወለዱ:: ትምህርታቸውን በሊሴ ገብረማርያም ለ12 ዓመታት ከተማሩ በኋላ ወደፈረንሳይ ሀገር በመሄድ ተምረው በጋዜጠኝነት በዲፕሎማ ተመርቀዋል:: ወደሃገር ከተመለሱም በኋላ በተለያየ የጋዜጠኝነትና በዲፕሎማትነት ሙያ አገልግለዋል::  በግዜውም የወሬ ምንጭ የሚባል የዜና አገልግሎት መስርተው ከዋና ዳይሬክተርነት እስከ ረዳት ሚኒስትርነት ደረጃ ያገለገሉ ሲሆን በፈረንሳይ የአምባሳደር ምክትል፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ረዳት ሚኒስትር፣ በሮም የንጉሠ ነገስቱ አምባሳደር እና በቱኒዚያ አምባሳደር ሆነው መስራታቸው ተጠቃሽ ነው:: በደርግ የስልጣን ዘመንም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ የዓለም አቀፍ የእርሻ ልማት ፈንድ መስሪያ ቤት የመንግስታት ግንኙነትና የፖለቲካ ኃላፊ በመሆን ለረጅም አመታት አገልግለዋል::

አምባሳደር ዘውዴ ጡረታ ከወጡም በኋላ በታሪክ ተመራማሪነት እና በጸሐፊነት ታዋቂነትን ያተረፉ ሲሆኑ ያሳተሟቸው መጻህፍት፦”የኤርትራ ጉዳይ በቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት”፣ “ተፈሪ መኮንን ረዥሙ የሥልጣን ጉዞ” እና “የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት ታሪክ” ናቸው

Leave A Reply

Your email address will not be published.