Take a fresh look at your lifestyle.
Browsing Category

Soccer

የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዊሃ ሀገራቸው ከናይጀሪያ ስትጫወት ተሰላፊ ነበሩ

ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዊሃ ላይቤሪያ ከናይጀሪያ ጋር ባደረገችው የእግር ኳስ ጨዋታ ተሰልፎ መጫወቱ የበርካቶችን ቀልብ ስቧል። ትናንት ምሽት በሞኖሮቪያ በተደረገው የላይቤሪያና የናይጀሪያ የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዊሃ በ51 ዓመት እድሜው ለሀገሩ ተሰልፎ ተጫውቷል። የቀድሞው ዝነኛ የእግር ኳስ ተጫዋችና የአሁኑ የሀገር መሪ ዊሃ ለ79 ደቂቃዎች ተሰልፎ…

የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ድልድል ይፋ ሆነ

ትናንት ምሽት በሞናኮ በተካሄደው የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ድልድል ዕጣ የወጣ ሲሆን ዩራጓያዊው ዲያጎ ፎርላንና ብራዚላዊው ካካ የዕጣ አወጣጥ ስነ_ስርዓቱን መርተውታል። የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ 32 ክለቦች የሚሳተፉበት ሲሆን የዘንድሮው የ2018_2019 መርሃ ግብር የሚከተለውን ይመስላል። በምድብ አንድ፡ አትሌቲኮ ማድሪድ፤ ቦሪሽያ ዶርትሙንድ፤ ሞናኮ፤ ክለብ…

ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ ከ20 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ሁለተኛ ጨዋታዋን ዛሬ ትመራለች ተባለ

ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ ከሐምሌ 29/2010ዓ.ም ጀምሮ በፈረንሳይ እየተካሄደ በሚገኘው ዘጠነኛው የፊፋ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች የዓለም ዋንጫ ሁለተኛ ጨዋታዋን ዛሬ በመሐል ዳኝነት ትመራለች ተባለ። ዛሬ ከቀኑ 11፡30 ላይ በምድብ አራት ጀርመን ከሀይቲ የሚያደርጉትን ጨዋታ ኢትዮጵያዊቷ ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ በመሐል ዳኝነት ትመራለች ተብሏል። ሊዲያ…

ኢትዮጵያና ኤርትራ የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርጉ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከኤርትራ ጋር በነሐሴ ወር አጋማሽ አስመራ ላይ የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋል። ከወራት አሰልጣኝ አልባ ቆይታ በኋላ አብርሃም መብራቱን የብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ የሾመው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሁለቱን ሀገራት ወንድማማችነት ለማጠናከር በማሰብ አስመራ ከተማ ላይ የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ባሳለፍነው ሳምንት ደብዳቤ የላከ ሲሆን…

ጅማ አባ ጅፋር የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቻምፒዮን ሆነ

የዘንድሮው ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ጅማ አባ ጅፋር ሆኗል።ጅማ አባ ጅፋር የሊጉ አሸናፊ የሆነው የፕሪምየር ሊጉ 30ኛ ሳምንት አዳማ ከተማን  5 ለ0 አሸንፎ ነው። የፕሪምየር ሊጉ ኮኮብ ግብ አስቆጣሪ የጅማ አባጅፋሩ አኪኪ አፎላቢ ሆኗል።ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ወልዲያ እና አርባምንጭ ወደ ታችኛው ዲቪዚዮን ወርደዋል።

በሩሲያ ለአንድ ወር ሲካሄድ የቆየው የአለም ዋንጫ ነገ ይጠናቀቃል

በሩሲያ ሞስኮ ለአንድ ወር ሲካሄድ የነበረው 21ኛው የአለም ዋንጫ ነገ ምሽት ፍፃሜውን ያገኛል።ነገ እሁድ 12 ሰዓት ላይ ፈረንሳይ ከክሮሺያ በሚያደርጉት የዋንጫ ጫዋታ ይጠናቀቃል።ጫዋታውን አለም በጉጉት እየጠበቀው ሲሆን የአሸናፊነት ግምቱን ለፈረንሳይ እየሰጠ ይገኛል።ዛሬ በተደረገ የደረጃ ጫዋታ ቤልጀየም እንግሊዝን ሁለት ለዜሮ በመርታት ሦስተኛ ሆና አጠናቃለች።ከአራት ዓመታት…

ፋሲል ከነማ በአስመራ ከተማ ይጫወታል

ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ አሁን በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረውን ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከርና ደስታውን ለመግፅ ከኤርትራ አቻው ጋር የወዳጅነት ጫወታ በአስመራ ከተማ ለማካሄድ ያቀረበው ጥያቄ ዛሬ አውንታዊ ምላሽ አግኝቷል።የኤርትራ እግር ኳስ ቡድን ጥያቄውን በደስታ እንደተቀበለውና ቁርጥ ያለውን ቀንም በቅርቡ በሚዲያ እናሳውቃለን ብሏል።

ክርስትያኖ ሮናልዶ ሪያል ማድሪድን ለቀቀ

የአለማችን እግር ኳስ ኮኮብ ተጫዋች ክርስትያኖ ሮናልዶ ሪያል ማድሪድን መልቀቁ ታውቋል።የ33 ዓመቱ ክሪስትያኖ ሮናልድ ከ9 ዓመታት በኋላ ሪያል ማድሪድን ለቆ የጣሊያኑንን ጁቬንቱስ በ100 ሚሊዮን ዩሮ ዩሮ ሊቀላቀል ስምምነት መደረሱ ተዘግቧል። ክርስቲያኖ ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት ለመቆየት የተስማማ ሲሆን ሳምንታዊ ደመወዙም አምስት መቶ ሺህ እንደሚሆን…

ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድን ከኤርትራ ጋር የወዳጅነት ጫወታ ለማድረግ ጥያቄ አቀረበ

ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድን ከኤርትራ ጋር የወዳጅነት ጫወታ ለማድረግ ጥያቄ አቀረበ።የኢትዮ-ኤርትራን ግንኙነት ለማጠናከር ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ለኤርትራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ጥያቄ ማቅረቡን ዛሬ ይፋ ባደረገው ደብዳቤ አስታውቋል። የሁለቱ ሀገራት ህዝቦች በባህል፣በኢኮኖሚ እንዲሁም የጋብቻ ትስስር በሀዘን በደስታ የማይለያይ ቁርኝት በስፖርትም…

የሩሲያው የዓለም ዋንጫ ሁለት ጫዋታዎችን ዛሬ ምሽት ያስተናግዳል

በሩሲያ ሞስኮ የእየተካሄደ ያለው የ2018 የዓለም ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ሁለት ጫዋታዎች ዛሬ ቀጥለው ያመሻሉ።ኡራጓይ ከፈረንሳይ 11 ሰዓት ላይ የሚካሄድ ሲሆን ምሽት ሦስት ሰዓት ላይ ደግሞ ብራዚል ከቤልጀየም ይጫወታሉ።በብራዚልና ቤልጀየም መካከል የሚደረገው ጫዋታ በብዙዎች ዘንድ በጉጉት እየተጠበቀ ነው።