Take a fresh look at your lifestyle.

ኢትዮጵያችን ዛሬ እሚላስ እሚቀመስ ሲጠፋ የጣት ቀለበቷን አውጥታ እንደምሸጥ እናት ሆናለች!??! (ደረጀ ደስታ)

በሱዳን እሚገኙት የኢትዮጵያ አምባሳደር ግብጽ ሱዳንና ኢትዮጵያ ትልቁን የአባይ ግድብ በጋራ ይመርቃሉ ሲሉ ተናግረዋል። ምን ማለት ይሆን? ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሳዑዲ አረብያን ጎብኝተዋል። የሳዑዲ ልዑኮችም ኢትዮጵያ ወርደዋል። ሳዑዲም አል አሙዲን ለመፍታት ቃል ከመግባት ጋር፣ ሞቅ ያለ ገንዘብ ለኢትዮጵያ መስጠቷ ተሰምቷል። የሳዑዲ ፍላጎት ደግሞ እርሻና የኤሌክትሪክ ኃይል መሆኑ ተነግሯል።…

በባህርዳር ሲካሄድ የቆየው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አመራር አባላቱን መርጦ ጉባኤውን አጠናቀቀ

በትናንትናው ዕለት የመስራች ጉባኤውን በባህርዳር የጀመረው  የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ  ዛሬ ሕዝባዊ ወይይት አድርጎ ተጠናቀቀ:: (ዜናውን በቭዲዮ ካዩት የጀነራል ተፈራ ማሞን እና የንግስት ይርጋን ጉባኤው ላይ ያደረገቱን ንግግር አብረው ይመለከታሉ – እዚህ ይጫኑ) በባህርዳር ከተማ ሙሉአለም አዳራሽ በተደረገው በዚሁ ጉባኤ ንቅናቄው የአማራር አባላትን ምርጫ አካሂዷል:: በዚህም መሰረት…

ሜቴክ ከፍተኛ የሀብት ብክነት እንዳለበት አመነ

ያለ ጥናት የተመረቱ ከዘጠኝ ቢሊዮን ብር በላይ ማሽነሪዎች ለብክነት ተጋልጠዋል የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ከፍተኛ የሀብት ብክነትና የውጤታማነት ችግር እንዳለበት አመነ። ኮርፖሬሽኑ ይህንን ያስታወቀው ረቡዕ ግንቦት29 ቀን 2010 ዓም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለፓርላማ የመንግሥት ወጪ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት፣ ለተሰነዘረበት ከፍተኛ የሀብትብክነት…

በመከላከያ እና ደህንነት መስሪያ ቤቶች ተጨማሪ ለውጦች እንደሚደረጉ ታወቀ

ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙ በሁዋላ ነባር የመከላከያ አመራሮች እና የደህንነቱ ሹም ከስልጣን ተነስተዋል። ይህንን ተከትሎ በመከላከያ እና በደህንነቱ ተቋም የብሄር ተዋጽዖን ለመጠበቅ ሲባል የተለያዩ ከፍተኛ አመራሮች ከስልጣን እንደሚነሱ ታውቋል። ለረጅም አመታት የደህንነት ሹም በመሆን የሰሩት የህወሃቱ አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ በጄ/ል አደም ኢብራሂም እንዲተኩ የተደረገ ሲሆን፣…

የድጋፍ መግለጫ ለአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ምስረታ

ለአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አመራር እና መላው አባላት በዛሬው እለት ምስረታችሁን እውን በማድረጋችሁ ደስታችንን እየገለጽን መጭው የትግል ዘመናችሁ የተሳካ እንዲሆን እንመኛለን። እኛም የአንድ አማራ ንቅናቄ አባላትና ደጋፊዎች በምታደርጉት የትግል ጉዞ ሁሉ እንደ አንድ አማራ አብረናችሁ የምንቆም መሆኑን ስናበስር በታላቅ አማራዊጨዋነት ነው።የአማራ ሕዝብ የተደቀነበትን ሁለንተናዊ የህልውና አደጋ…

አገር በአማርኛ! (ስሜታዊ ጽሁፍ)-ደረጀ ደስታ

አማርኛ ጥሩ ነገር ነው። “አማራ አለ ወይስ የለም?” የሚያስብል የመከራከሪያ ቋንቋ ነው። እኛ እንቶኔዎች አማሮች እንዴት እንደጨቆኑን የምንናገረው በአማርኛ ነው። እኛ ጎንደሮች ከጎጃሞች ስለመሻላችን ጎጃሞችም ከጎንደሮች ስለመብለጣችን ወሎዬዎች ስለቁንጅናችን... የምናወራው በአማርኛ ነው። ሸዋ “ምነው ሸዋ!” የሚለው በአማርኛ ነው። ጉራጌም አማራን የሚያቄለው በአማርኛ ነው። አዲስ አበባም…