Take a fresh look at your lifestyle.

ጎንደር ከተማ የሀገር ሽማግሌዎችን መምረጧ ተገለጸ

የጎንደር ከተማ እና የአካባቢው  ነዋሪዎች ከየትኛውም የመንግስትና የፖለቲካ ፓርቲ ነፃ የሆነ 13 አባላትን የያዘ የሀገር ሽማግሌዎችን ዛሬ ሐምሌ 23/2010ዓ.ም በርካታ ህዝብ በተሳተፈበት ስብሰባ ተመርጠዋል።

ሽማግሌዎች በከተማዋ ጉዳይ ሕዝብን አስተባብረው እንደሚሰሩ ተገልፆአል።የአገር ሽማግሌዎችም ከዚህ ቀደም እንደነበሩት በመንግስት እጂ አዙር ተጠምዝዘው የመንግስት ተልዕኮ አሰፈፃሚዎች እንዳይሆኑ የከተማው ህዝብ በአደራ ጭምር እንዳሳሰባቸው ተነግሯል።

ዛሬ የተመረጡት የአገር ሽማግሌዎችም ሰም ዝርዝር:_

 1. አቶ ባዮ በዛብህ
 2. አቶ ዳዊት ደርበው
 3. አቶ ሙሉቀን ሲሳይ
 4. ሀጂ ማሩፍ
 5. አቶ አለማየሁ መኳንነት
 6. አቶ ሲሳይ አሰማረ
 7. አቶ ጌጡ ታደሰ
 8. አቶ ወሰንጌ ታደሰ
 9. አቶ ሹምየ ወ/ሰላሴ
 10. ኢንጂነር በወቀቱ
 11. ወ/ሮ የሺ ደሴ
 12. አቶ ምሰጦፋ
 13. አቶ መንገሻ ዘውዱ ናቸው

በሌላ በኩል በሰ/ጎንደር ጭልጋ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ከፍተኛ ተኩስ እንዳለና መኖሪያ ቤቶችም በእሳት እየተቃጠሉ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ጠቁሟል።

በሰሜን ጎንደር ዞን ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ በህወሓት ጠንሳሽነት የአካባቢውን ነዋሪ “አማራና ቅማንት” በማለት ርስ በርስ እንዲጋጭ ብሎም አካባቢው የሞት ቀጠና እንዲሆን እየሰራ እንደሚገኝ የሚታወስ ነው።

Leave A Reply

Your email address will not be published.