Take a fresh look at your lifestyle.

የሻደይ፣አሸንድየ እና ሶለል በዓል አከባበር ዝግጅት መጠናቀቁን የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ገለጸ

የሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል በዓልን በደመቀ ሁኔታ በክልሉ ከተሞች ለማክበር ዝግጅቱ መጠናቀቁን የአማራ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡ የክልሉ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ልዑል ዮሐንስ ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በሠጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ‹‹በዓሉን ከምንጊዜውም በላይ በደመቀ ሁኔታ በክልሉ የተለያዩ ቦታዎች ለማክበር ዝግጀቱን አጠናቀናል ›› ነው ያሉት፡፡ ከነሐሴ 16 እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2010 ዓ.ም የሚከበረው የሻደይ፣ የአሸንድየ እና የሶለል በዓል በሁለት ዙር ይከበራል ተብሏል፡፡ የመጀመሪያው ዙር ከነሐሴ 16 እስከ ነሐሴ18 ቀን በዋግ ኸምራ ሰቆጣ- የሻደይን ፣ በላስታ ላሊበላ- የአሸንድየን እና በራያ ቆቦ- የሶለል በዓላትን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁን አቶ ልዑል ገልጸውልናል፡፡ በሁለተኛው ዙር ደግሞ ከነሐሴ 19 እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ በክልሉ ርዕሰ መዲና ባህር ዳር የሻደይ፣ የአሸንድየ እና የሶለል በዓላት ይከበራሉ ነው ያሉት፡፡ የአዲስ ዓመት ብስራት ዋዜማ፣ የልጃገረዶች የነፃነት ቀን እና የመንፃት በዓል የሆነው ይህ በዓል በቀጣይም የሀገሪቱ የገቢ ምንጭ ለማድረግም አልሞ መስራትን ይጠይቃል መባሉን የአማራ ቴሌዥን ዘግቧል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.