Take a fresh look at your lifestyle.

አንበሳ አውቶብስ ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር እንዲሆን መወሰኑ ተገለጸ

የአንበሳ አውቶብስ ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር እንዲሆን መወሰኑ ተገለጸ።ም/ ከንቲባ ታከለ ኡማ ስልጣን ከተረከቡ ወዲህ በወሰዷቸው የተለያዩ  የለውጥ( Reforms) ስራዎች መካከል ወደ ፌዴራል መንግስቱ ዞረው የነበሩ መስሪያቤቶችን ወደ ከተማ አስተዳደሩ መመለስ ነው።በመሆኑም ለአዲስ አበባ ከተማ ለበርካታ ዓመታት የትራንስፖርት በመስጠት የሚታወቀው አንበሳ አውቶብስ ድርጅት ወደ ከተማ አስተዳደሩ እንዲመለስ መደረጉ ተገልጿል።

የአንበሳ አውቶብስ ድርጅት ቀደም ሲል በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር ይተዳደር ነበር፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በወሰነው ውሳኔ መሠረት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስና  በስሩ ሲተዳደር የቆየው የጅማ ከተማ አንበሳ አውቶብስ ድርጅትም ራሱን ችሎ እንዲደራጅ ተወስኗል።

ከአዲስ አበባ ከተማ ወደ ፌዴራል መንግሥት እንዲዛወሩ ከተደረጉ ተቋማት ውስጥም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለሥልጣን፣ እንዲሁም አንበሳ የከተማ አውቶብስ ድርጅትና ከትራንስፖርት ጋር የተያያዙ የተለያዩ አሠራሮች ተጠቃሾች ናቸው፡፡ይሁን እንጂ ውሳኔው በተለያዩ መሰናክሎች ተግባዊ ሳይደረግ ቆይቶ፣ በሥራ አመራር ቦርድና በፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ሲመራ ቆይቷል፡፡

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.