Take a fresh look at your lifestyle.

በአዳማ ከተማ የተፈናቃዮች መጠለያ ትናንት በተነሳ ግጭት በርካታ ሰዎች መጎዳታቸው ተገለጸ

በአዳማ ከተማ የተፈናቃዮች መጠለያ ትናንት በተነሳ ግጭት በርካታ ሰዎች መጎዳታቸው ተገለጸ።በቅርቡ ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለው በአዳማ ከተማ መጠለያ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ከአካባቢው ነዋሪ ጋር በተፈጠረ ግጭት መጠለያቸው በእሳት ሲቃጠል፤ 40 የሚሆኑ ተፈናቃዮች ከባድና ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች አመልክተዋል።በግጭቱ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን በአዳማ ሆስፒታል የሦስተኛ ዓመት የቀዶ ሕክምና ፕሬዝዳንት ዶክተር ድዳ ባቱ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።

በግጭቱ ምክንያት መጠለያ ጣቢያዎች በእሳት የወደሙባቸው ተፈናቃዮች በሀይማኖት ተቋማት ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ታውቋል።የሀይማኖት ተቋማት  ይጠቃሉ የሚል ስጋት ያደረባቸው የከተማው ነዋሪዎችና ፖሊስ በከተማው ዙሪያ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን በመጠበቅ ላይ መሆኑ ተሰምቷል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.