Take a fresh look at your lifestyle.

በቂሊንጦ እስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል

በቂሊንጦ የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች ከትላንት ጀምረው ለምን አንፈታም በሚል ተቃውመው እያሰሙ ነው።የምግብ አድማም እንደጀመሩ ታውቋል።በአሁን ሰዓት ከውስጥ እስረኞች ከውጭ ደግሞ ቤተሰቦቻቸው ከፍተኛ ጩኸት እያሰሙ ነው።

የአዲስ አበባ ፖሊስ የእስረኛ ቤተሰቦችን በመደብደብ ከአካባቢው ለማራቅ እየሞከረ ነው።

እስካሁን ድረስ በምን ምክንያት እንዳልተፈቱ የማይታወቅ 100 የሚሆኑ በአግ7 እና ኦነግ አባልነት ተጠርጥረው የሽብር ክስ የቀረበባቸው እስረኞች በቂሊንጦ ይገኛሉ።

Leave A Reply

Your email address will not be published.